News  

Nov 5, 2020

የአማራ ልማት ማህበር በታላቋ ብሪታኒያ (አልማ ዩኬ) በአማራ ክልል የሚኖሩ አቅመ ደካሞችንና በጣም ዝቅተኛ ገቢ ያላቸዉ ወገኖችን ከኮቪድ-19 ለመከላልከል የሚደረጉትን ጥረት ለማገዝ በጎፈንድሚ ሶስት ሺ አምስት መቶ ሰላሰ አንድ (3,531) የእንግሊዝ ፓዉንድ አሰባስቦ ገንዘቡን ሙሉ በሙሉ ወደ አልማ ኢትዮጵያ በ28/09/2020 እ.ኤ.አ አስተላልፏል ።

የአማራ ልማት ማህበር በኢትዮጵያም በ12/10/2020 እ.ኤ.አ አንድ መቶ ስልሳ አምስት ሺ (165,000) የኢትዮጵያ ብር በላይ በሆነ ወጭ ለ አንድ መቶ (100) የሚሆኑ አቅመ ደካሞችና ዝቅተኛ ገቢ ላላቸዉ ወገኖቻችን በነፍስ ወከፍ የሚከተሉትን አከፈፍሏል ፥

  • 1ኛ/ ታጥቦ ጥቅም ላይ የሚዉል የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል
  • 2ኛ/ ግማሽ ሊትር የንፅህና መጠበቂያ ፈሳሽ (sanitazer)
  • 3ኛ/ 3 ሊትር የምግብ ዘይት
  • 4ኛ/ 25 ኪሎ ግራም የፍርኖ ዱቄት

በዚህ አጋጣሚ ገንዘባችሁን፣ ጉልበታችሁን እና ጊዜያችሁን በመለገስ ለተባበራችሁን ወገኖቻችን በሙሉ በተረጅዎችና በአልማ ዩኬ ስም ከፍተኛ ምስጋና እናቀርባለን።
አልማ ዩኬ

ለተጨማሪ መረጃ ይህን ቪዲዮ ይመልከቱ።




May 3, 2020

Please help us to support some of the most vulnerable people in rural Amhara region of Ethiopia as they fight the spread of COVID-19

The Amhara Development Association in the United Kingdom (ADA-UK) is calling upon all its members and supporters to raise Fifteen Thousand Pounds (£15,000) through GoFundMe to support the effort of the people in the Amhara Region of Ethiopia to curtail the spread of COVID-19.

The money will be used to purchase urgent sanitation equipment and will be distributed to elderly and low-income people in rural areas. Please kindly donate as generously as you can. ADA-UK would like to thank you in advance for your generous donation and support in this difficult time. Your generosity will save lives.

About ADA-UK:
ADA-UK is a registered charity in England and Wales (no 1141100) from 1 April 2011 and it is a membership-based charity run entirely by volunteers. The current membership is socially diverse and consists of mainly Ethiopians and British of Ethiopian origin who reside in the UK.

ADA-UK objects are:

  • To promote education for the public in the Amhara region of Ethiopia, with special attention to primary education.
  • To promote health for the public in the Amhara region of Ethiopia, with special attention to primary healthcare and mother and child healthcare with an emphasis on health education and prevention.

It is our aim to make knowledge, experience and resources more accessible to help people build a better life in the Amhara region of Ethiopia.

Thank you so much for your generous support.


For further info please contact us on

T: 07908819346
Email: enquiries@amharadevelopment.org


በአማራ ክልል የሚኖሩ አቅመ ደካሞች እና በጣም ዝቅተኛ ገቢ ያላቸዉ ወገኖቻችንን COVID-19ን ለመከላከል የሚያደርጉትን ጥረት ለማገዝ በምናደርገዉ የገንዘብ ማሰባሰብ እባክዎን ይርዱን።

የአማራ ልማት ማህበር በዩናይትድ ኪንግደም (አልማ-ዩኬ) የኮቪድ 19ን ስርጭትን ለመግታት በአማራ ክልል የሚደረገዉን እንቅስቃሴ በመደገፍ ከአባሎቹ እና ከበጎ አድራጊ ግለሰቦች በቀጥታ እና በጎፈንድሚ የገንዘብ ድጋፍ አሥራ አምስት ሺ ፓዉንድ (£15,000) ለማሰባሰብ ሥራ ጀምሯል።

የሚሰበሰበው ገንዘብ ንፅህናን ለመጠበቅ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን መግዣነት የሚውል ሲሆን በገጠሩ አካባቢ ለበሽታው ተጋላጭ ለሆኑ አቅመ ደካሞችን እና በጣም ዝቅተኛ ገቢ ላላቸዉ ወገኖቻችን የሚከፋፈል ይሆናል። እባክዎን በሚችሉት አቅም የገንዘብ ድጋፍ ያደርጉ ዘንድ እንማፀንዎታለን። እያንዳንዷ የሚታበረክቷት የገንዘብ ልግስና የወገኖቻችንን ሕይወት ይታደጋልና ለመልካም ተግባርዎ አልማ-ዩኬ አስቀድሞ ከልብ ያመሰግናል።

አልማ-ዩኬን በተመለከተ:
አልማ-ዩኬ (የቻሪቲ ቁጥር 1141100) እ.ኤ.አ ሚያዚያ 1 ቀን 2011 በእንግሊዝ እና በዌልስ የተመዘገበ እና ሙሉ በሙሉ በበጎ ፈቃደኞች የሚደገፍ የበጎ አድራጎት ድርጅት ነው፡፡ በአባልትነት ያካተታቸው በተለይ በታላቋ ብሪታኒያ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ትዉልደ ኢትዮጵያዊያን ናቸው።

የአልማ-ዩኬ አላማ:

  • በአማራ ክልል ለህዝብ ትምህርትን ማስፋፋት እና ማጎልበት፤ ልዩ ትኩረቱም አንደኛ ደረጃ ትምህርት ላይ ነዉ።
  • በአማራ ክልል የህብረተሰብ ጤና ጥበቃን ማስፋፋትና እና ማጎልበት፤ ልዩ ትኩረቱም ለእናቶች እና ለሕፃናት የመጀመሪያ ደረጃ ጤና ጥበቃ ላይ ነዉ።

ተባብረን በአማራ ክልል የሚገኙ ወገኖቻችን የተሻለ ኑሮ ለመገንባት በሚያደርጉት ጥረት በእውቀት ፣ በተሞክሮ እና በሀብት ለመደገፍ እንስራ፡፡

ለትብብርዎ ሁሉ ከልብ እናመሰግናለን

Fight the spread of COVID-19 in the Amhara region GoFundMe

Links
Amhara Development Association (ADA)
Contact Us
Contact Us
Archive
ADA-UK 2013
ADA-UK 2011
ADA 1992 - 2010 (Amharic)
Part 1 (pdf)
Part 2 (pdf)
Part 3 (pdf)
Part 4 - coming soon
Part 5 (pdf)
Part 6 (pdf)
Part 7 (pdf)
Part 8 (pdf)
Part 9 (pdf)
Part 10 (pdf)
Part 11 (pdf)
Part 12 (pdf)
making knowledge, experience and resources more accessible to help people build a better life
Amhara Development Association - UK (ADA - UK) is a registered charity in England and Wales (no 1141100)